በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህወሓት 45 ዓመት ሆነው


"የፌደራል መንግሥት ከውጭ ኃይሎች ተመሳጥሮ የትግራይ ሰላም ለማወክ እየሰራ ነው" ሲሉ የህወሓት ሊቀምንበርና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ።

ዶ/ር ደብረፅዮን ይህንን ያሉት የህወሓት ምስረታ 45ኛ ዓመት የካቲት 11 በዛሬው ዕለት በመቀሌ ከተማ በተከበረበት ግዜ ነው።

በንግግራቸው "በአሁኑ ግዜ በዕኩልነት የተመሰረተ አንድነት በመከተል መጓዝ ይስፈልጋል ካልሆነ የትግራይ ህዝብ በትግሉ ያመጣው መብቱ እጁ ላይ ነው ያለው" ብለዋል።

በዚህ ጉድይ ምላሽ የጠየቅነው የብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያ መንግሥት ለምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት የሚሰራ እንጂ ለትግራይ ሰላም መደፍረስ ይሰራል የተባለው መሰረተ ቢስ ነው ብልዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ህወሓት 45 ዓመት ሆነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:21 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG