በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህወሓት ከሕጋዊ ፓርቲነት ተሰረዘ


የህወሓትን ሕጋዊ ሰውነት መሰረዙን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ፓርቲው ሃይልን መሠረት ያደረገ የአመፃ ተግባር ላይ መሳተፉን እንዳረጋገጠ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

የፓርቲው ሃላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ውሳኔ ማሳለፉንም ነው ቦርዱ ያስታወቀው።

በትግራይ ክልል የሚገኙ ሌሎች ሦስት ፓርቲዎችም ስለ እንቅስቃሴያቸው ማብራሪያ እንዲሰጡ ትዕዛዝ መስጠቱትን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ባይቶና እና ሳልሳይ ወያኔ የተባሉት ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምዝገባ ሂደት ላይ እያሉ፣ በትግራይ ክልል በተካሄደ ሕገወጥ ምርጫ ስለመሳተፋቸው እንደዚሁም የፓርቲው አመራሮች በአመጻ ተግባር ስለመሳተፋቸው መረጃ እንደደረሰው ነው ቦርዱ የገለጸው።

የአሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም እንደዚሁ በሕገወጥ ምርጫ ስለመሳተፉ መረጃ እንደደረሰው ቦርዱ በመግለጫው ጠቅሷል።

XS
SM
MD
LG