በሰሜን አሜሪካና አውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከቅርብና ከሩቅ ተጠራርተው ቅዳሜለት በአርሊንግተን ቨርጂኒያ ስብሰባ አድርገው ነበር። ውይይታቸው በኢትዮጵያ ዘለቄታ ያለው ትብብር ለመገንባት የሚያስችሉ አዳዲስ ሃሳቦችና የጋር እሴቶችን በመመርመር ላይ ያተኮረ ነበር።
በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የተባለ የሲቪክ ድርጅት ያሰናዳው ጉባዔ ከተለያዩ ብሄሮች፤ ጾታና የሃይማኖት አባላት፤ እራሳቸውን እንደግለሰብ ወክለው የተሳተፉበት ነበር።
ቅዳሜለት በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ በምትገኘው አርሊንግተን ቨርጂኒያ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያዊያን፤ በሀገራቸው ተቋማዊ አስተዳድር ባልተጠናከረበት መልኩ፤ ማህበረሰቦች ሊጫወቱት የሚገባቸው ሚና፣ እንዲሁም እርስ በርስ የመተባበር ሃሳቦች ላይ ያተኮረ ነው።
የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ ያሰናዳው የማህበረሰብ ውይይት፤ በኢትዮጵያ በመከባበር ላይ የተመሰረተ፤ ህዝባዊ ትብብርና የጋራ እሴት ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ መንገድ፣ አዲስ የትብብር ስልቶች አስፈላጊ እንደሆኑ ተሳታፊዎቹ ውሏቸውን የተወያዩበት ጉዳይ ነው።