በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሥቃይ አያያዝ ተጎጂዎች ቀን ታስቦ ዋለ


ሰኔ 19 በዓለም ዙሪያ የሥቃይ አያያዝ ተጋላጭና ተጎጂ የሆኑ ሰዎችን ለመደገፍና የሥቃይ አያያዝንም ለመዋጋት የተወሰነ ዓለምአቀፍ ዕለት ነው፡፡

የዘንድሮው ሰኔ 19 በዚሁ የሥቃይ አያያዝ ወይም ቶርቸር ጉዳይ ላይ የመከረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባዔ 25ኛ ዓመት ነው፡፡

ዋና ፅሕፈት ቤቱ ኮፐንሃገን - ዴንማርክ የሚገኘው የሥቃይ አያያዝ ተጎጂዎችን የማቋቋም ዓለምአቀፍ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ብሪታ ሲድሮፍ ዛሬ በሰጡት መግለጫ “ስለመልሶ ማቋቋም ስናወሣ አስፈላጊም ነው፤ በዓለምአቀፍ ሕግ መሠረት መብትም ነው፡፡ ሥቃይ የደረሰባቸው ሰዎች ሁለገብ እየሆነ የመልሶ ማቋቋም ማለትም የአዕምሮ ፈውስና የደህንነት መብት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ የህክምና አገልግሎት ማግኘት አለባቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜም በተለየ ሁኔታ የሥነ አዕምሮ አገልግሎት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሥቃይ የፈፀመባቸውን የመንግሥት አካል ወይም የመንግሥት ተቋም ለፍርድ ለማቅረብ ሕጋዊ እርዳታ የሚያስፈልግበት ጊዜ አለ፡፡ በተጨማሪም የገንዘብም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውም አሉ” ብለዋል፡፡

በዓለም ዙሪያ ያለውን የሥቃይ አያያዝ ችግር በተመለከተ መሻሻሎች እየታዩ መሆናቸውን ዋና ፀሐፊዋ ብሪታ ሲድሆፍ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG