በካናዳው የG20 ስብሰባ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን መገኘት አስመልክቶ በቶሮንቶ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ።
የተቃውሞውን ሰልፍ የጠራው በቶሮንቶና አካባቢው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ሲሆን አንድነት ለሰብአዊ መብቶችና ለዴሞክራሲ፣ የፖለቲካ እስረኞች ድጋፍ ኮሚቴ፣ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ደጋፊዎችና ኢሕአፓ ዴሞክራቲክ ተባባሪ አዘጋጆች መሆናቸው ተገልጿል። ከኦጋዴን የሰብአዊ መብት ኮሚቴም በተቃዋሚ ሰልፍ ላይ የተገኙ ተወካይ ነበሩ።
አቶ የሱፍ ኡመር የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ግብረ-ኀይል ቃል አቀባይ “ሰላማዊ ሰልፉን የጠራነው በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ወከባ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሚዲያ አፈና የአለም ሕዝብ እንዲያውቀው በተለይም እዚህ የተሰበሰቡ የG20 መሪዎች እንዲያውቁ ነው፣” ብለዋል።
ሰልፉ ላይ የተገኙት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንኳን ጠቅላላ አፍሪቃን ኢትጵያን ሊወክሉ አይገባም የሕዝብ መብት ረጋጭ ናቸውና ብለዋል።
ከዚህ ሰልፍ ጎን ለጎን አቶ ኪዳነ-ማርያም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካናዳ ጉባኤ ላይ መገኘት የኢትዮጵያን ክብር ከፍ ያደረገ ስለሆነ የድጋፍ ሰልፍ አድርገናል ብለዋል።