በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቴኔሲ ክፍለ ግዛት የደረሰው ከባድ ዝናብ ያዘለ አውሎ ንፋስ የሰው ህይወት አጠፋ


ዩናይትድ ስቴትስ ቴኔሲ ክፍለ ግዛት ዛሬ ማክሰኞ ንጋት ላይ የደረሰው ከባድ ዝናብ ያዘለ አውሎ ንፋስ ቢያንስ አስራ ዘጠኝ ሰው ገደለ። ከባድ የንብረት ውድመት አስከትሏል።

አንደኛው አውሎ ነፋስ መብረቅ ቀላቅሎ በናሽቪል ከተማ መሃል ህንፃዎችን እያፈራረሰ ሲነጉድ ታይቷል። በከተማዋ ዙሪያ ቢያንስ አርባ ህንፃዎች መውደማቸውን ተነግሮን ለዕርዳታ ተንቀስቅሰናል ሲሉ የአጣዳፊ ሁኔታ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ናሽቪል ውስጥ ቢያንስ ሁለት ሰዎች እንደሞቱ ነው የተገለፀው። የፖለቲካ ነክ ጉዳዮች ታዛቢዎች እንደሚናገሩት የደረሰው አደጋ ዛሬ የዲምክራቲክ ፓርቲው ፕሬዚዳንታዊ ዕጩ ቅድመ ምርጫ ከሚካሄድባቸው አስራ አራት ክፍለ ግዛቶች አንዷ በሆነችውን በቴኔሲ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ ሳያስተጓጉል አይቀርም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG