በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዴሞክራሲያዊ ኮንጎ የሰላም አስከባሪ ኃይሉ ተጠንቅቆ እና ፈጥኖ እንዲወጣ ተመድ አሳሰበ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪዎች በኮንጎ
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪዎች በኮንጎ

በግጭት በታመሰችው ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚገኙ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪዎች፣ በተቻለ ፍጥነት እና ጥንቃቄ በታከለበት መንገድ ለቀው መውጣት እንዳለባቸው፣ የድርጅቱ የሰላም ማስከበር ሥራዎች ምክትል ዋና ጸሐፊ ዣን ፒየር ላክሮክስ አሳሰቡ።

በዋና ከተማዪቱ ኪንሻሳ፣ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ፒየር፥ የኮንጎ መንግሥት ለታጣቂ ኃይሎች የሚሰጠው ምላሽ፣ “ለሞት የሚዳርግና የደኅንነት ክፍተት እንዳይፈጥር” አስጠንቅቀዋል፡፡

እ.ኤ.አ ከ1999 ጀምሮ፣ በዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተሠማራው፣ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ኃይል፣ በዓመት ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ በጀት የተመደበለት፣ በዓለም ካሉት ታላላቅ የሰላም አስከባሪ ሥምሪቶች መካከል አንዱ እንደኾነ፣ አጃንስ ፍራንስ አመልክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሰላም አስከባሪ ኃይሉ፣ ወደ 16ሺሕ የሚደርሱ፣ ዩኒፎርም የለበሱ ሠራተኞች ሲኖሩት፤ አብዛኞቹ፣ በማዕድን በበለጸገውና ዐማፅያን ለሦስት ዐሥርት ዓመታት በሚንቀሳቀሱበት፣ የምሥራቅ ኮንጎ አካባቢ ተመድበው ተልዕኳቸውን በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ፣ የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG