በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ እና የቻይና ባለሥልጣናት ሰሜን ኮሪያን ሊጎበኙ ነው


ጦርነቱ ያበቃበትን በዓል የሚዘክረውን ብሄራዊ የፎቶ ኤግዚቢሽን እየጎበኙ በፒዮንግያንግ፣ ሰሜን እ አ አ ሐምሌ
ጦርነቱ ያበቃበትን በዓል የሚዘክረውን ብሄራዊ የፎቶ ኤግዚቢሽን እየጎበኙ በፒዮንግያንግ፣ ሰሜን እ አ አ ሐምሌ

ሰሜን ኮሪያ፣ በያዝነው ሳምንት፣ የሁለቱ ኮሪያዎች ጦርነት ያበቃበትን የጦር ስምምነት ዓመታዊ በዓል ለማክበር፣ ወደ ፒዩንግያንግ የሚያቀኑትን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር እና የቻይና ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ተቀብላ እንደምታስተናግድ አመለከተች።

እንደ አገሪቱ ብዙኃን መገናኛ ዘገባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ በከፍተኛ ባለሥልጣናቱ ጉብኝት፣ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ለረዥም ጊዜ ዘግታ የቆየችውን ድንበሯን ለመክፈት ማቀዷን የሚያሳይ ምልክት ሊኾን ይችላል።

“በመከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ የሚመራው የሩሲያ ፌዴሬሽን ወታደራዊ ልዑክ፣ ለኮሪያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊት ሪፑብሊክ፣ የደስታ ስሜት መግለጫ ጉብኝት ያደርጋል፤” ሲል፣ መንግሥታዊው የኮሪያ ማዕከላዊ የዜና አገልግሎት፣ በዛሬው ዕለት ዘግቧል። የቻይና ልዑካን ቡድንም፣ ከነገ በስቲያ ኀሙስ በሚካሔደው ሥነ ሥርዐት ላይ እንደሚገኝ፣ የዜና አገልግሎቱ ከአንድ ቀን በፊት ባቀረበው ዘገባ አረጋግጦ ነበር።

ከፒዩንግያንግ ታሪካዊ አጋሮች አንዷ የኾነችው ሩሲያ፣ የዩክሬኑን ወረራዋን በጽናት ከደገፉት መሪዋ ኪም ጆንግ ዑን ጋራ ያላቸውን ጥብቅ ወዳጅነት ከቀጠሉ በጣት የሚቆጠሩ አገሮች አንዷ ናት።

በተያያዘ፣ ኪም ጆንግ ዑን ለሩሲያ ባሳዩት ድጋፍ፣ “ሮኬቶችንና ሚሳዬሎችን ለሞስኮ አቅርበዋል፤” ስትል፣ ዋሽንግተን መወንጀሏ ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG