የዩናይትድ ስቴትሱ ብሔራዊ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ጄክ ሱሊቫን ከቻይናው ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋንግ ዪ ጋር ዛሬ ቤጂንግ ላይ ተገናኝተው የሚያደርጉት ውይይት ‘ውጤታማ ይሆናል’ የሚል ተስፋ ማሳደራቸውን ተናገሩ።
ዛሬ ከቀትር በኋላ ቤጂንግ የገቡት ሱሊቫን ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ጋር "ውጤታማ” ያሉትን ውይይት ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ጨምረው ገልጠዋል። "በምንስማማባቸውም ሆነ በሌሎችመጠነ ሠፊ ጉዳዮች ዙሪያ ልዩነቶቻችንን ተጨባጭ በሆነ መንገድ መመልከት የሚያስችል ውጤታማ ውይይት እናደርጋለን” ብለዋል።
በተመሳሳይም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ‘አዎንታዊ’ እና ‘ውጤታማ’ እንደሚሆን ተስፋ ለጣሉበት ውይይት ዝግጁ መሆናቸውን እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2016 ወዲህ ቤጂንግን ሲጎበኙ የመጀመሪያው ለሆኑት የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ ጉዳዮች አማካሪ ነግረዋቸዋል።
በሌላ ዜና የዋሽንግተን አጋር የሆኑት ጃፓን እና ፊሊፒንስ በቅርቡ በክልሉ የሚታየውን ውጥረት በማባባስ ቻይናን ተጠያቂ አድርገዋል። ቶኪዮ ቤጂንግ የአየር ክልሌን ጥሳለች በሚል ስትወነጅል፤ ማኒላ በበኩሏ የደቡብ ምሥራቅ እስያን ሰላም በማወክ ‘ዋናዋ አገር ነች’ ስትል ከሳታለች።
መድረክ / ፎረም