በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኡጋንዳ የመብት ተሟጋች ቡድኖች የኢንተርኔት ህጉን በመቃወም ክስ መሰረቱ


ፎቶ ፋይል - የዲጂታል አክቲቪስቶች በካምፓላ፣ ዩጋንዳ
ፎቶ ፋይል - የዲጂታል አክቲቪስቶች በካምፓላ፣ ዩጋንዳ

የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ባላፈው ወር የፈረሙበት “አዲሱ የኢንተርኔት ህግ የመናገር ነጻነትን ለመግታት እና የመንግሥት ተቃዋሚ ቡድኖችን ዒላማ ያደረገ ነው” ሲሉ በኡጋንዳ የመብት ተሟጋቾች ድርጅቶች እና የህግ ባለሙያዎች ጥምረት የመሰረቱትን ክስ ዛሬ ለፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡

አዲሱ ህግ “ኮምፒውተርን ያለአለግባብ መጠቀም” በሚለው ድንጋጌው በኡጋንዳ ህግ የተከለከሉ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ማተም፣ ማሰራጨትና ማጋራትን እንዲሁም የደብቅ፣ ያልተገለጸና የሀሰት ማንነትን በድረ ገጽ ላይ መጠቀምን ይከለክላል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል “አስጨናቂ” ሲል የተቸው የህግ ማሻሻያ እንዲሰረዝ ጠይቋል፡፡

በኡጋንዳ 9 የመብቶች ቡድኖችን ያካተተው ጥምረት፣ በፓርላማው የተቃዋሚዎች ቡድን መሪ የነበሩትና ሶስት እውቅ የህግ ባለሙያዎች፣ አቤቱታቸውን ዛሬ ሀሙስ ለህገ መንግሥታዊው ፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡

የማሻሻያ ህጉ የህግ ተቃውሞ ሲቀርብበት ሁለተኛው ጊዜ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በኡጋንዳ ቻፕተር ፎር የሚባለው ታዋቂው የመብቶች ተሟጋች ቡድን ህጉ አሻሚና ግልጽ ባልሆነ መንገድ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያና ድረገጾች ላይ ያላቸውን ባህርይ ይቆጣጠራል ሲል ተችቷል፡፡

ጋዜጠኞችም ስለሚዘግቧቸው ሰዎች መረጃ ለመሰብሰብ የትኛውን መስመር መተላለፍ እንደማይገባቸው ግልጽ አለመሆኑንም ድርጅቱ አመልክቷል፡፡

ህጉን ተላልፎ የተገኙ ሰዎች ለ10 ዓመታት የመንግሥትን ሥልጣን መያዝ እንደማይችሉ የተደነገገ ሲሆን፣ እስከ 3ሺ900 ወይም 15 ሚሊዮን የዩጋንዳ ሽልንግ ቅጣት፣ ከሰባት ዓመት እስር ጋር እንደሚጠብቃቸ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG