በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

(ማረሚያ)የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር በአዲስ አበባ መግለጫ የመስጠት እቅድ አልነበራቸውም


ታም ማሊኖውስኪ
ታም ማሊኖውስኪ

ረቡዕ ታኅሣስ 5/2007 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የገባው በዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ታም ማሊኖውስኪ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቡድን ትናንት ረፋድ ላይ መግለጫ ሊሰጡ በዕቅድ ተይዞ እንደነበርና ሊሰጡት የነበረው መግለጫ መሰረዙን ጠቅሰን የዘገብነው ስህተት ስለሆነ "መግለጫ የመስጠት እቅድ አልነበረም" በሚል ይታረም።

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳስታወቀው ፤ ኢትዮጵያ የገባው በዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ታም ማሊኖውስኪ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቡድን ትናንት ረፋድ ታኅሣስ 6/2009 ላይ መግለጫ የመስጠት እቅድ እንዳልተያዘ።

ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ሚስተር ማሊኖውስኪና የቡድናቸው አባላት በሰብዓዊ መብቶችና በአስተዳደር ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ኢትዮጵያ ገብተዋል። ይኸው በረዳት ሚኒስትር ማሊኖውስኪ የተመራ የሰብዓዊ መብቶች ቡድን በተጨማሪም ከሲቪል ማኅበረሰብና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተጠሪዎች ጋር ሊገናኝ በዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ስብሰባዎቹ ይካሄዱ አይካሄዱ እንደማይታወቅም የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ መረጃ አክሎ ጠቁሟል፡፡

ቡድኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚቆየው እስከ ከነገ በስተያ፤ ቅዳሜ ታኅሣስ 8 እንደሚሆን ታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG