የቶጎ ገዥ ፓርቲ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር በተካሄደው የፓርላማ ምርጫ አብላጫውን መቀመጫ አሸነፈ።
“የፕሬዝዳንት ፎር ኛሲንግቤን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም የተወሰደ እምርጃ አካል ነው” በሚል በተቃዋሚዎች ተቀባይነት የተነፈገውን ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት የምርጫ ኮሚሽኑ ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል።
ከትናንት በስተያ፤ ቅዳሜ ምሽት የወጣው ውጤት ገዥው ዩኒየን ፎር ዘ ሪፓብሊክ (የሪፓብሊኳ ኅብረት) ፓርቲ ከ113 መቀመጫዎች 108ቱን ማሸነፉን ይናገራል።
አዲሱ ህገ መንግሥታዊ ማሻሻያ በፕሬዝዳንታዊ የሥልጣን ዘመን ላይ ለውጥ አድርጎ አንድ ፕሬዚዳንት ለሁለት ባለ አራት ዓመታት ዘመኖች መመረጥ እንደሚችል ስለሚደነግግ ከ1997 ዓ.ም. የ57 ዓመቱ ኛሲንግቤ የአሁን ዘመን ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ሲያበቃ እንደገና ለስምንት ዓመታት በሥልጣን ላይ እንዲቆዩ እንደሚያስችላቸው ተዘግቧል።
የገዥው ፓርቲ ቃል አቀባይ ጊልበርት ባዋራ ለአሶሲየትድ ፕሬስ በሰጡት ቃል "ቶጎዊያን በግልፅ ደግፈውናል" ብለዋል።
ምዕራብ አፍሪካዊቱን ሃገር ለአርባ ዓመታት የገዙትን አባታቸውን ኢያዴማን የተኩት ፎር ኛሲንግቤ ቶጎን ሃያ ዓመታት ለሚሆን ጊዜ እየመሩ ነው።
ተቺዎች እንደሚሉት “ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያው የኛሲንግቤን ቤተሰብ ስርወ መንግሥት ያስቀጥላል።”
መድረክ / ፎረም