በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቲለርሰን ማክሰኞ አዲሳባ ናቸው


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ከፊታችን ማክሰኞ የካቲት ሃያ ሰባት አንስቶ ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ ሃገሮችን እንደሚጎበኙ መሥሪያ ቤታቸው አስታውቋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ከፊታችን ማክሰኞ የካቲት ሃያ ሰባት አንስቶ ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ ሃገሮችን እንደሚጎበኙ መሥሪያ ቤታቸው አስታውቋል።

ቲለርሰን አፍሪካን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸው ሲጎበኙ የመጀመሪያቸው የሚሆነውን ጉዞ የሚጀምሩት በአዲስ አበባ ሲሆን ቀጥለውም ወደ ኬንያ፣ ጂቡቲ፣ ናይጄሪያ እና ቻድ እንደሚጓዙ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ሄዘር ኑዌርት ቢሮ የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ዩናይትድ ስቴትስ ከአፍሪካ መንግሥታትና ህዝቦች ጋር ያላትን አጋርነት ለማጎልበት ከሚጎበኟቸው ሃገሮች መሪዎችና ከአፍሪካ ኅብረት ኃላፊዎችም ጋር ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ ስለጉዟቸው የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

መግለጫው አክሎም “ሚኒስትሩ በተለይ ሽብርተኝነትን በመዋጋት፣ ሰላምና ፀጥታን፣ እንዲሁም መልካም አስተዳደርን በማጠናከር፣ የጋራ ንግድና ኢንቬስትመንትን በማሳደግ፣ ከአጋሮቻችን ጋር መሥራት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ያተኮረ ውይይት ለማድረግ ዕቅድ አላቸው” ብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን በሚጎበኟቸው ሃገሮች ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲዎች ሠራተኞችን እንደሚያነጋግሩና የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ድጋፍ የሚያደርግላቸው የሥራ እንቅስቃሴዎችን በሚያሳዩ ዝግጅቶች ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG