በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሬክስ ቲለርሰን የሳውዲ አረብያና የኢራቅ መንግሥታት ጉባዔ ሊሳተፉ ነው

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ዛሬ አርብ ወደመካከለኛው ምሥራቅ ይጓዛሉ። ሚኒስትሩ የሳውዲ አረብያና የኢራቅ መንግሥታት በሚያካሂዱት ታሪካዊ ጉባዔ ላይ ይገኛሉ። የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ማሻሻል የሚያስችሉ መንገዶችን ይፈትሻሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ዛሬ አርብ ወደመካከለኛው ምሥራቅ ይጓዛሉ። ሚኒስትሩ የሳውዲ አረብያና የኢራቅ መንግሥታት በሚያካሂዱት ታሪካዊ ጉባዔ ላይ ይገኛሉ። የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ማሻሻል የሚያስችሉ መንገዶችን ይፈትሻሉ።

ግንኑነታቸው ሻል እያለ የመጡት ሪያድ እና ባግዳድ የሚያካሂዱት የመጀመሪያ የአስተባባሪ ምክር ቤታቸውን ስብሰባ መሆኑ ታውቁዋል። ስብሰባው ዩናይትድ ስቴትስ ኢራቅን ይበልጡን ከሪያድ እንድትቀራረብ በማድረግ ኢራቅ ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የኢራን ተፅዕኖ ለመቀነስ የያዘችው ጥረት አከል ተደርጎ ተወስዷል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሄዘር ኖርት ትናንት ለጋዜጠኞች ባደረጉት ገለፃ

“ኢራን ምንጊዜም ቢሆን ስጋታችን ነች፣ ይህ ስጋታችን ደግሞ ኢራቅ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በክልሉ ነው።” ብለዋል።

ስብሰባው የሚካሄደው ሪያድ ውስጥ ሲሆን ሚኒስትር ቲለርሰን በሪያድ ቆይታቸው ከተለያዩ የሳውዲ ባለሥልጣናት ጋር ስለየመን ጦርነት፣ ስለኢራንና ሌሎችም አስፈላጊ የሆኑ የክልሉና የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ይነጋገራሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG