በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሬክስ ቲለርሰን የአፍጋኒስታን ጉብኝት


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ዛሬ በአፍጋኒስታን በአካሄዱት አስቀድሞ ያልተገለፀ ጉብኝት ከሀገሪቱ መሪዎች ጋር ስለ አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የደቡብ እስያ ስትራቴጂ ተነጋግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ዛሬ በአፍጋኒስታን በአካሄዱት አስቀድሞ ያልተገለፀ ጉብኝት ከሀገሪቱ መሪዎች ጋር ስለ አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የደቡብ እስያ ስትራቴጂ ተነጋግረዋል።

ቲለርሰን መካከለኛው ምሥራቅንና ደቡብ እስያን በሚጎበኙበት በአሁኑ ወቅት ከአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋኒ፣ ከዋናው ኃላፊ አብዱላ አብዱና ከሀሪቱ የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪ ሐኒፍ አትማር ጋር ዛሬ ተገናኝተው ተነጋግረዋል ሲሉ የአፍጋኒስታን መሪዎች ገልፀዋል።

“ዩናይትድ ስቴትስ ለደቡብ እስያ ያላት አዲስ ስትራቴጂ በአፍጋኒስታን ሰላም ለማውረድና ይህን አላማ አደጋ ላይ የሚጥሉ አሸባሪዎችን መጠጊያ ለማሳጣት ስትል ከአፍጋኒስታን መንግሥትና በክልሉ ካሉት አጋሮች ጋር ለመሥራት ያላትን ቁርጠኛነት ያስያል” ሲሉ የውጭ ጉድይ ሚኒስትሩ ቲለርሰን ገልፀዋል።

የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት ጋኒ በበኩላቸው ለአዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ስትራቴጂ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል። መንግሥታቸው መላ የአፍጋኒስታን ህዝብ ሰላማና ደህንነት እንዲጠበቅ የሚያስችል ለውጥ ለማድረግ የወሰነ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ቲለርሰን በዩናይትስድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት አፍጋኒስታንን ሲጎበኙ ለመጀመርያ ጊዜ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG