በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ስለሮሒንግያ ሙስሊሞች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ሚያንማርን በጎበኙበት ወቅት የፀጥታ ኃይሎችና በራሳቸው አነሳሽነት የሚንቀሳቀሱ ወገኖች የሮሒንግያ በተባለው ክፍለ ሀገር ውስጥ ሰፊ የጭካኔ ተግበር ይፈጽማሉ የሚባለው ተዓማኒ ወሬ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። ይሁንና ማዕቀብ እንዲጣል እንደማመክሩ አስገንዝበዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ሚያንማርን በጎበኙበት ወቅት የፀጥታ ኃይሎችና በራሳቸው አነሳሽነት የሚንቀሳቀሱ ወገኖች የሮሒንግያ በተባለው ክፍለ ሀገር ውስጥ ሰፊ የጭካኔ ተግበር ይፈጽማሉ የሚባለው ተዓማኒ ወሬ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። ይሁንና ማዕቀብ እንዲጣል እንደማመክሩ አስገንዝበዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በውሁዳኑ የሮሒንግያሙስሊሞች ላይ ይፈፀማል ስላለው የዘር ማፅዳት ተግባር ቲለርሰን ሲናገሩ በግለሰቦች ላይ ያተኮረ ማዕቀብ መጣሉ ተገቢ ሊሆን ይችልላ። አጠቃላይ ማዕቀብ መጣል ግን ቀውሱን በመፍታት ረገድ ሲረዳ አይታየኛም” ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከሀገሪቱ መሪ ኦንግ ሳን ሱቹ ጎን ሆነው ነው። ዩናይትድ ስቴትስ ለሮሒንግያ ስደተኞች ተጨማሪ 47 ሚልዮን ዶላር እንደምትሰጥ በማስታወቅ “ሚያንማር እንዲስካላት እንፈልጋለን” ብለዋል።

በአጠቃላይ በያዝነው አመት አሜሪካ ለሮሂንጋ ስደተኞች የሰጠችው ገንዘብ $87 ሚልዮን ዶላር ደርሷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG