በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቲክቶክ ኃላፊ ኮንግረስ ይቀርባሉ


ቲክቶክ
ቲክቶክ

የቲክቶክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሹ ዚ ቼው የፊታችን መጋቢት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት የኃይልና የንግድ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተገለፀ።

ቼው መጋቢት 14/2015 ዓ.ም. ምክር ቤቱ ኮሚቴ ፊት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚቀርቡ የኮሚቴው ሊቀመንበር ሪፐብሊካኑ እንደራሴ መክሞሪስ ሮጀርስ ዛሬ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

“የቲክቶክ ባለቤት የሆነው ባይትዳንስ ኩባንያ የቻይና ኮምዩኒስት ፓርቲ የአሜሪካዊያን ተጠቃሚዎችን መረጃ እንዲያገኙ ሆን ብሎ ይፈቅዳል” ያሉት መክሞሪስ “አሜሪካዊያን ይህ፣ የግል ገመናቸውንና መረጃዎችን ምን ያህል እንደሚነካ የማወቅ መብት አላቸው” ብለዋል።

የዋና ሥራ አስፈፃሚው የውጭ ጉዳይ ኮሚቴው ፊት የመቅረብ ዜና የወጣው ኮሚቴው ከብሄራዊ ደኅንነት ጋር በተያያዘ ቲክቶክ በዩናትድ ስቴትስ ውስጥ የሚሰጠው አገልግሎት እንዲታገድ በቀረበው የህግ ረቂቅ ላይ በሚቀጥለው ወር ድምፅ ለመስጠት ዕቅድ በተያዘበት ጊዜ መሆኑ ተመልክቷል።

ቼው በምክር ቤቱ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ቃላቸውን እንደሚሰጡ ቲክ ቶክ ዛሬ ሰኞ በሰጠው መግለጫ አረጋግጧል።

XS
SM
MD
LG