በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ መንግሥት ለትግራይ ቀውስ 305 ሚሊዮን ዶላር ረድቷል


የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት(ዩ ኤስ ኤድ) በትግራይ ተረጅዎችን እየረዳ ነው፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት(ዩ ኤስ ኤድ) በትግራይ ተረጅዎችን እየረዳ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (ዩ ኤስ ኤድ) በትግራይ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጭ ቡድን መሪ የሆኑት፣ ኤምሊ ዴኪን፣ በትግራይ ክልል ተጎጂ ለሆኑ ተፈናቃዮች አስፈላጊውን የሰብአዊ እርዳታዎችን እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካ መንግሥት እስካሁን በክልሉ ባለው ግጭት ተጎጂ ለሆኑ ሰዎች እርዳታ የሚውል ወደ 305 ሚሊዮን ዶላር ማውጣቱንም አስረድተዋል፡፡ የቡድን መሪዋን ያነጋገረው የቪኦኤ ትግርኛ ክፍል ባልደረባችን በትረ ሥልጣን ከላከልን ዘገባ ተከታዩን አጠናቅረናል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (ዩ ኤስ ኤድ)፣ በትግራይ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጭ ቡድን መሪ ፣ ኤምሊ ዴኪን በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል፣ በግጭቱ የተጎዱ ወገኖችን ብዛትም ሆነ የሁኔታውን አሳሳቢነት በመግለጽ፣ ድርጅታቸውም ሆነ አጋሮቻቸው በመስጠት ላይ የሚገኙትን ሰብአዊ እርዳታ እንደሚቀጥሉበት ተናግረዋል፡፡

“በተለይ በሽሬ አካባቢ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የተፈናቃይ ህዝብ ክምችት እንዳለ እናውቃለን፡፡ ስለዚህ እነዚያ ሰዎች በስፍራው እንደደረሱም የሚያስፈልጋቸው የነፍስ አድን አቅርቦት ሁሉ እንዲያገኙ ብዙ ጥረት” ይደረጋል በማለት ተከታዩን ብለዋል፡፡

“በአሁኑ ወቅት ትግራይ ውስጥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግምት መሠረት፣ በጠቅላላው ወደ 4.5 ሚሊዮን ሰዎች የሰብአዊ እርዳታ እንደሚሹ እናውቃለን፡፡ ያ በጣም እጅግ ከባድ የሆነ ሥራ ነው፡፡ ስለዚህ ከአጋሮቻችን ጋር ሆነን የህይወት አድን እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ በትክክል ተደራሽ መሆናችንን በማረጋገጥ መስራታችንን ቀጥለናል፡፡”

የአሜሪካ መንግሥት ለትግራይ ቀውስ 305 ሚሊዮን ዶላር ረድቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:12 0:00

በአሁኑ ሰዓት “እርዳታ ለመስጠት በማይቻልበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን እናውቃለን” ያሉት ኤምሊ፣ ያም በጣም አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እርዳታ ወደ ሚያስፈልጋቸው ወደ እነዚህ ሰዎች ዘንድ ለመድረስና፣ አጋሮቻችንም የሚያገኟቸው መሆኑን ለማረጋገጥ፣ በኤምባሲያችን በኩል፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየሠራን ነው ብለዋል፡፡

አንዳንድ ችግሮች አሉ፣ ተረጅዎችን አጋሮቻችን በቀላሉ ሊያገኛዋቸው የሚችሉባቸው አካባቢዎች፣ በትላልቅ ከተሞችና ከዋና ዋና መንገዶች አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ነው፡፡ ካሉ በኋላ፣ ስለሆነም “ እርዳታው አቅርቦት ሊደረስባቸው ባልተቻለባቸው አካባቢዎች በመድረስ፣ እርዳታውን ላላገኙ ሰዎች ለመድረስ እንዲቻል፣ ከተባበሩት መንግሥታት አጋሮች ድርጅቶች ጋር እየተሠራ” መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በኣጠቃላይ ግን ለህዝቡ በሚያስፈልገው የእርዳታ መጠንና ዓይነት የተነኩ መሆኑንም ሃልፊዋ ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል

“በተለያዩ ዘርፎች የምግብ ዋስትና የተመጣጠነ ምግብ የጤና ንጽህንና የንጹህ ውሃ በሌሎች ዘርፎች ያሉትን ጨምሮ በሚያስፈልጉ ሰብአዊ እርዳታዎች ብዛት ዓይነትና መጠን ተነክተናል፡፡ ከአጋሮቻችን ጋር ሆነን እርዳታው በቀጥታ ከሚያስፈልጋቸው ጋር በቀጥታ በመገናኘት ውጤታማ በሆነ መንገድ በምንመድበው ገንዘብም ሆነ በምንሰጠው እርዳታ ልንረዳቸው የምንችልበትን መንገድ በማፈላለግ ጠንክረን ሠርተናል፡፡” ብለዋል፡፡

ለሰአብዊው እርዳታ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት፣ እስካሁን ወደ 305 ሚሊዮን ዶላር ለግሷል፡፡ ያሉት ኃላፊዋ፣ ይህ እርዳታ በጣም አስፈላጊ ለሆኑ የምግብ እርዳታዎች፣ ለውሃ፣ ለመድሃኒት አቅርቦት፣ በክልሉ ውስጥ ለተፈናቀሉ ሰዎች፣ ደህንነቱ የተጠበቀ መጠለያ ማቅረብና ከግጭት አካባቢዎች የሚሸሹ ሰዎችንም ደህንነት ለመጠበቅ የሚረዱ፣ የተለያዩ ድጋፎችን ለመስጠት የዋለ ነው፡፡” በማለት ተናግረዋል፡፡

ለመጠለያ እንዲውሉ በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ ስለገቡት እቃዎችም የተደሰቱ መሆኑን ኃላፊዋ እንደሚከተለው ገልጸዋል፡፡

“ትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ተጎጂ ለሆኑ ከ82ሺ,000 በላይ ሰዎች ለሚቀልሷቸው የአስቸኳይ ጊዜ መጠለያዎች መከለያ የሚሆን፣ 1ሺ500 ጥቅልና ጠንካራ የፕላስቲክ መሸፈኛዎችን በአውሮፕላን ከዱባይ አጓጉዘን አዲስ አበባ በማስገባታችንም ደስ ብሎናል፡፡ እነዚህን ወደ መቀሌ ሽሬ እና እርዳታው እጅግ በጣም ወደሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች እናጓጉዛለን፡፡”

“ከምናደርጋቸው ሌሎች ነገሮች ብዙ ሰብሎች መውደማቸውንና የሰዎችና የገበያ ቦታዎች መስተጓገላቸውን ተገንዝበናል፡፡ ብዙ ሚሊዮን ሰዎች ቤቶቻቸውን ለቀው እንደተሰደዱም ይታወቃል፡፡” ያሉት የዩኤስ ኤድ ኃላፊ ኤምሊ ዴኪን፣ በምግብ አቅርቦት በኩል ለተረጅዎቹ አሁን እየተደረገ ያለውን ድጋፍ እንደሚከተለው ዘርዝረዋል፡፡

“አሁን የምንሰጠውን የምግብ እርዳታ በማጠናከር ወደ አንድ መቶ ስድስት ሺ ሜትሪክ ቶን ስንዴ፣ የምግብ ዘይት እንዲሁም ልዩ የተመጣጠነ ምግብ ከዚያ ውስጥ ወደ 4 ሚሊዮን ህዝብ በተመጣጠነ የምግብ እጥረት የተጎዱ ወደ 400ሺ የሚደርሱ ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ መመገብ የሚችል ነው፡፡ ከአጋሮቻችንም ጋር በመሆን ወደ 140ሺ ለሚሆኑ ሰዎች ንጽሁ የመጠጥ ውሃ ለማዳረስ እንዲሁም የንጽህና መጠበቂያ ቁሶችን እና የውሃ መቅጃና ማጠራቀሚያ እቃዎችን ለማቅረብ እየሠራን ነው፡፡”

“አጋሮቻችንን የመድሃኒት አቅርቦትን ደህንነታቸው በተጠበቀ ስፍራ እንዲያኖሩና ለሴቶችና ህጻናት የምክር አገልግሎቶችን በመስጠት እንዲሁም በግጭቱ የተነሳ፣ ከወላጆቻቸው የተነጠሉ ህጻናትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር መልሶ በማገናኘት እንዲሁም ቀደም ሲል እንደገልጽኩት የመጠለያ ፍላጎቶችን ለማሟላት ከኢትዮጵያ መንግስትና ከሰብአዊ እርዳታ ሰጭ አጋር ድርጅቶቻችን ጋር በመሆን፣ ከክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን በሽሬና አካባቢው ለማስፈር የሚረዱ መጠለያዎችን እየሠራን ነው፡፡” በማለት ዩኤስ ኤድ በትግራይ እያደረገ ያለውን ነገር ዘርዝረውዋል፡፡

በትግራይ የዩ ኤስ ኤድ፣ የአደጋ ጊዜ የእርዳታ ምላሽ ሰጭ ቡድን፣ ድርጅታቸው በሱዳን የተጠለሉትን ስደተኞችንም እንደሚረዱ ተናግረዋል፡፡

“ዋነኛው ትኩረታችንን ያደረግነው ኢትዮጵያ ውስጥ በትግራይ ክልል ለቀሩት ይሁን እንጂ፣ በሱዳን ያሉትን ስደተኞችን ከዓለም ምግብ ድርጅት አማካይነት አጣዳፊ የምግብ እርዳታዎችን እንሰጣለን” ብለዋል፡፡

እስካሁን በትግራይ ውስጥ በሚሰጡት ሰብአዊ አገልግሎት ሊጠቅሱት የሚችሉት ምንም ዓይነት ችግር ያልደረሰባቸው መሆኑን የገለጹት፣ የዩኤስ ኤድ ሓላፊዋ ኤምሊ ዴኪን፣ “በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በኩል፣ ለትግራይ ህዝብ ትልቅ ድጋፍ ያለ ይመስለኛል፡፡ እርዳታችንንም የምቀጥልበት ሲሆን ከአጋሮቻችን ጋር በመስራት የሚሰጠው ሰብአዊ እርዳታ በሚያስፈልገው መጠን መሟላቱን ለማረጋገጥ፣ ሌሎች ለጋሽ ድርጅቶችም፣ በክልሉ ላለው ችግር እርዳታቸውን እንዲለግሱ እናበረታታለን፡፡” ማለታቸውን፣ ከቪኦኤ ትግርኛው ክፍል የተላከልን የበትረ ስልጣን ዘገባ ያስረዳል፡፡

XS
SM
MD
LG