ዋሺንግተን ዲሲ —
የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ዴምህት/ አመራሮች ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል።
የገቡ በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ በመመልከት ባደረጉት ውሳኔ እንደሆነ ተናግረዋል። ለለፋና ኮርፖሬሽን መግለጫ የሰጡ የድርጅቱ ዋና ጸሓፊ አቶ ግደይ አሰፋ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ እይተካሄደ ያለውን ለውጥ እንደሚደግፉና ድርጅቱ ከአሁን በኋላ ትግሉን በሰላማዊ መንገድ ለመቀጠል መወሰኑን አመልክተዋል።
“ከሃያ ሰባት ዓመት በፊት በረሃ የወጣነው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ባለመቻላችን ነው ሲሉም አክለዋል። የድርጅቱን አመራሮች በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር አክሊሉ ሃይለ ሚካኤል አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ