በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች መውጣታቸው ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ ዩኒቨርስቲ
ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ ዩኒቨርስቲ

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ካሉ አራት ዩኒቨርሲቲዎች 10 ሺሕ 164 ተማሪዎችን ማስወጣቱን አስታወቀ።

ከክልሉ ከወጡ ተማሪዎች መካከል ለአሜሪካ ድምጽ አስተያየታቸውን የሰጡ ተማሪዎች፣ የህወሓት ኃይሎች ክልሉን ከተቆጣጠሩ በኋላ ከምግብ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ቀስ በቀስ እጥረት እየተከሰተ ስለመምጣቱ ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ህዝቡ ከጎናቸው ሆኖ ሲተባበራቸው እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡ ተማሪዎቹ ከዚህ በኋላ ወደ ነበሩበት ዩኒቨርሲቲ ተመልሰው ትምህርታቸውን የመከታተል ፍላጎት እንደሌላቸውም ተናግረዋል፡፡

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርረት ሚኒስቴር በዛሬ መግለጫው፣ የ2013 ዓ.ም ተመራቂ የሆኑ የመቀሌ፣ የአክሱም እና የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያልተጠናቀቀ የትምህርት ተግባራቸውን የሚያጠናቅቁበትንና የሚመረቁበትን ሁኔታ እንደሚያመቻች አስታውቋል፡፡

ከተመራቂዎች ውጭ ስላሉ ተማሪዎች ግን በመግለጫው ላይ የተባለ ነገር የለም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች መውጣታቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:02 0:00


XS
SM
MD
LG