በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የህወሓት መሪዎች "ከ10 ሺህ በላይ ወታደር ማረክን" ይላሉ


ፎቶ ፋይል፦ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካዔል
ፎቶ ፋይል፦ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካዔል

- ተከዜ የአውሮፕላን ድብደባ ተፈፅሞበታልም ብሏል - ፌዴራል መንግሥቱ መረጃው "ውሸት ነው" ብሏል

በትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት “ከ10 ሺሕ በላይ ሰራዊት ማርከናል” ብለዋል የትግራይ ክልል መሪ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል።

“ከተማረኩት ውስጥ ኤርትራዊያንም ይገኙባቸዋል” - ብለዋል።

ዶ/ር ደብረጽዮን በሰጡት ማብራሪያ የፌደራል መንግሥት የትግራይ ሕዝብ የኤሌትሪክ አቅርቦት እንዳያገኝና በጨለማ እንዲኖር ኃይል ከማቋረጥ ተሻግሮ፤ “የተከዜ ኃይል ማመንጫና የኤሌትሪክ ማከፋፈያ በአውሮፕላን ደብድቦ ጉዳት አድርሷል” በማለት ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማጣሪያ፤ የትግራይ ክልል መንግሥት ተከዜ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ መደብደቡን መግለፁን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ፤ ዝርዝሩን ሲያስረዳ፤ “ልክ እንደ ሌሎቹ የኃይል ማመንጫ ግድቦች ሁሉ በፌዴራል መንግሥት ተገንብቶ የሚተዳደረው ግድብ እሁድ ጥቅምት 29/2013 ዓ.ም የህወሓት ሚሊሻ ግድቡን ለመጠበቅ የተሠማራውን የፌዴራል ፖሊስ ኃይል ከሥራው ለማደናቀፍ ጥቃት ፈጽሟል” ይላል።

“የተጎዱት እና የተገደሉት ቁጥር ያልተረጋገጠ ቢሆንም፣ በሕይወት የተረፉት 11 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ለ14 ሰዓት ያህል በእግር ተጉዘው፣ ተራራዎችን አቆራርጠው ወደ ጎንደር ገብተዋልም” ብሏል መግለጫው።

“በቀጣዮቹ ቀናት የህወሓት አክቲቪስቶች በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት "ግድቡን ተቆጣጥረናል" የሚል መረጃ ማሰራጨታቸው ተስተውሏል።” ይላል መግለጫው።

ዝርዝሩን በሚያስረዳበት ክፍልም፤ “ነገር ግን አምነስቲ ኢንተርናሽናል የህወሓት ሚልሻዎች በማይካድራ በንጹሀን ዜጎች ላይ የፈፀሙትን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ሪፖርት ባወጣበት ኅዳር 3/2013 ዓ.ም፣ የህዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር የተከዜ ግድብ በቦንብ እንደተመታ የሚያትት ሆን ተብሎ የተቀናበረ፣ የሀሰት መረጃን ህወሓት በቴሌቪዥን አሰራጭቷል። ባለ ሁለት ክበብ ቅስት ያለው እና በውሀ የተሞላ ግድብ በቦንብ ቢመታ ሊያስከትል የሚችለው መጥለቅለቅ እና ጥፋት ማንም ሊገምተው የሚችለው መሆኑ የመረጃውን ሀሰተኛነት በቀላሉ ለማረጋገጥ ይቻላል” በማለት የትግራይ ክልሉን መረጃ አስተባብሏል።

ዶ/ር ደብረጽዮን ተማረኩ ያሉትን ኤርትራዊያን በተመለከተ፤ ከኤርትራ ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ዋሺንግተን ዲሲ ያለው የኤርትራ ኤምባሲ ለጊዜው በኮቪድ-19 ምክንያት ዝግ መሆኑ ተነግሮናል፤ ይሁን እንጂ በዚህ ሣምንት መጀመሪያ ላይ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል “ይህ የውስጥ ግጭት ነው፤ በግጭቱ ውስጥ የለንበትም” ማለታቸው አይዘነጋም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

የትግራይ ክልል ከ10 ሺሕ ጦር በላይ መማረኩን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:57 0:00


XS
SM
MD
LG