መቀሌ —
ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚያገናኙ የሑመራ - ኡምሓጀርና የራማ -ዓዲዃላ የመንገድ መስመሮች በቅርብ ግዜ ተከፍተው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ለማጠናከር ውይይት አመራሮች እያካሄድን ነው አሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በትናንትናው ዕለት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ:በክልሉ ደቡባዊና ምዕራባዊ ዞኖች ስላካሄዱት ጉብኝት ማብራርያ ሰጥተዋል።
በትግራይና አማራ ክልሎች ግንኙነት ለማጠናከር የህዝብ ለህዝብና የአመራሮች ግንኙነት መፍጠር ስራ በአዋሳኝ አከባቢዎች እየተፈፀመ ነው ብለዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ