የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ተካሮ፣ ዛሬ በዓዲግራት ከተማ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ይገባኛል ጥያቄ ውዝግብ መፍጠሩ ተገለጸ።
በዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን፣ ለዓዲግራት ከተማ የሾማቸውን ከንቲባ፣ ጽሕፈት ቤቱን በኃይል በመስበር አስገብቷል ሲል ፣ የትግራይ ምስራቃዊ ዞን የፀጥታ ሓላፊ አቶ ኪዱ ገብረ ፃድቅ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
በዛሬው ዕለት ከንቲባው ጽሕፈት ቤት ገቡ የተባሉት፣ አቶ ረዳኢ ገብረ እግዚአብሔር፣ “ወደ ጽሕፈት ቤቱ በር ሰብረን አልገባንም፣ ህዝብ በምክርቤት የተመረጠ ከንቲባ ይግባ ብሎ በሰልፍ ስለመጣ ነው ወደ ፅሕፈት ቤት የገባነው ብለዋል።
በሌላ ዜና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት፣አቶ ጌታቸው ረዳ ሦስት የትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦችን አገዱ።
በትላንትናው ዕለት በአቶ ጌታቸው ረዳ ፊርማ የተጻፈ ደብዳቤ፣ ሜጀር ጄነራል ዮሐንስ ወ/ጊዮርጊሰ፣ ሜጀር ጄነራል ማሾ በየነ እና ብርጋዴር ጄነራል ምግበይ ኅይለ በጊዜያዊነት ታግደዋል በማለት ያስረዳል።
ውሳኔው በደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን እና የክልሉ የፀጥታ እና ሰላም ቢሮ ተቃውመውታል።
መድረክ / ፎረም