በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ እንደሰጉ ነዋሪዎች ገለጹ


ፎቶ ፋይል፦ መቐለ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ መቐለ ከተማ
በትግራይ ክልል ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ እንደሰጉ ነዋሪዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:25 0:00

በትግራይ ክልል የሚገኙ ወታደራዊ አመራሮች ትላንት በሰጡት መግለጫ በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ለሚመራው ህወሓት ቡድን ድጋፍ እንደሚሰጡ መግለጻቸውን ተከትሎ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች፣ ትግራይ ክልል ዳግም ወደ ጦርነት እንዳትገባ የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናገሩ። ሁለቱም ወገኖች ጉዳዩን ወደ ሕዝብ አቅርበው “ይዳኙ” ብለዋል።

በሌላ በኩል ሦስት የክልሉ ፓርቲዎች በሰጡት መግለጫ፣ የወታደራዊ አመራርን በፖለቲካዊ ጉዳዮች ጣልቃ መግባት እንደሚቃወሙ በመግለጽ፣ “ወታደራዊ አዛዦቹ ከኤርትራ መንግሥት ድጋፍ ያላቸው ናቸው" በማለት ወንጅለዋል።

ከከፍተኛ ወታደራዊ ጄነራሎች አንዱ፣ ኮልኔል ገብረ ገብረ ጻድቃን፣ “የትግራይ የፀጥታ ሁኔታ ከትግራይ ሕዝብ እና የፀጥታ አካል ውጭ ባለመኾኑ የውጭ ኃይል አንሻም" ሲሉ ውንጀላውን አጣጥለዋል። አክለውም "ጉዳዩ ስም ማጥፋት ነው” ብለዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG