በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ የፌደራል ፖሊስ አባላት - ለ3 ዓመታት ያለ ደመዎዝና ስራ ተቀምጠናል


መቐለ ከተማ
መቐለ ከተማ
በትግራይ የፌደራል ፖሊስ አባላት - ለ3 ዓመታት ያለ ደመዎዝና ስራ ተቀምጠናል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:37 0:00

የፌደራሉ መንግስት፣ትግራይን ለማረጋጋት በሚል፣በ2013 ዓ/ም በክልሉ ያሰማራቸው የክልሉ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ከሦስት አመታት በላይ ያለ ደመዎዝና ስራ ተቀምጠናል ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡

መንግስት በተጠቀሰው አመት ሰኔ ወር ላይ፣መቀሌን ለቆ ሲወጣ፣ ትቷቸው መውጣቱን የጠቀሱት እነዚሁ 465 የፖሊስ አባላት፣ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ለፌደራል ፖሊስ ያቀረቡት ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱን ጠቅሰዋል፡፡

በጉዳዩ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከኢትዮጵያ ዕንባ ጠባቂ ተቋምና ከመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

የፌደራል ፖሊስ፣ ታህሳስ 29 ቀን 2016 ዓ/ም. ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የጻፈውና የአሜሪካ ድምፅ የተመለከተው ደብዳቤ ግን፣የተጠቀሱት መኮንኖችና አባሎች ወደ ተቋሙ ያልተመለሱት፣ በዲሲፕሊን ጉድለት ወይም "ኩብለላ" ብሎ በገለፀው ጥፋት ተከሰው መሆኑን ጠቅሷል።

"ቅድሚያ ለሰብአዊ መብት" የተባለ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ግን የፖሊስ አባላቱ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ወደ ስራ ገበታቸው መመለስ ይገባቸዋል ብሏል::

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG