በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲፓ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ


መቀሌ
መቀሌ

የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር ጉዳይ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥረት ማድረግ ከዓላማዎቹ መሆኑን ትግራይ ክልል ውስጥ ይካሄዳል በተባለው ምርጫ እንደሚሣተፉ ካሳወቁት አራት አዳዲስ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የአሲምባ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር አቶ ዶሪ አስገዶም ገልፀዋል።

ከሁለቱ ሃገሮች መንግሥታት ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

“አለ” ለሚሉት የመልካም አስተዳደር መጓደል፣ የትምህርትና የጤና ችግሮች መፍትኄ ለማግኘት ድርጅታቸው እንደሚጥርም ገልፀዋል።

“አሲምባ ዲሞክራስያዊ ፓርቲ አዲስ እንደመሆኑ መጠን በምርጫው የምንሳተፈው ለማሸነፍ ሳይሆን በክልሉ ምክር ቤት ውስጥ መቀመጫ ለማግኘት ነው” ብለዋል አቶ ዶሪ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አዲፓ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:19 0:00


XS
SM
MD
LG