በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና “የተሻለ ውጤት የተገኘው በቁጭትም” እንደኾነ ክልሉ ገለጸ


በትግራይ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና “የተሻለ ውጤት የተገኘው በቁጭትም” እንደኾነ ክልሉ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:07 0:00

በትግራይ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና “የተሻለ ውጤት የተገኘው በቁጭትም” እንደኾነ ክልሉ ገለጸ

በትግራይ ክልል፣ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች፣ 66ነጥብ96 በመቶ ተፈታኞች፣ ከግማሽ በላይ ነጥብ ማስመዘገባቸውን፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሓላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዑሽ አስታውቀዋል፡፡

የቢሮው ሓላፊ “የተሻለ” ሲሉ የገለጹትን የፈተና ውጤት ማስመዝገብ የተቻለው፣ ቀደም ሲል ተማሪዎቹ፣ የ10ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ያለፉና ለፈተናው መቀመጥ ከሚገባቸው ዕድሜ በአራት ዓመት ዘግይተው በመፈተናቸው የተማሪዎቹ ብስለት በመጨመሩ እንደኾነ፣ ሓላፊው አስረድተዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው ጋራ ሲነጻጸርም እንዴት የተሻለ ውጤት እንደተገኘ የተጠየቁት ሓላፊው፣ “ተማሪዎቹ በጦርነቱ በደረሰባቸው ችግር፣ መድረስ ከሚገባን ደረጃ ወደ ኋላ ቀርተናል፤ በሚል ቁጭት እና ወኔ በዩኒቨርሲቲዎች ጭምር ገብተው በአጭር ጊዜ ዝግጅት ስላደረጉ እንደኾነ” አስረድተዋል፡፡ 657 ነጥብ ከፍተኛ ውጤት ኾኖ እንደተመዘገበም፣ ሓላፊው አክለው ተናግረዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG