በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአክሱም ሴት ተማሪዎች ሒጃብ እንዳይለብሱ የተደረገውን ክልከላ የሚቃወም ሰለፍ በመቐለ ተካሔደ

በአክሱም ሴት ተማሪዎች ሒጃብ እንዳይለብሱ የተደረገውን ክልከላ የሚቃወም ሰለፍ በመቐለ ተካሔደ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:31 0:00

በአክሱም ሴት ተማሪዎች ሒጃብ እንዳይለብሱ የተደረገውን ክልከላ የሚቃወም ሰለፍ በመቐለ ተካሔደ

የአክሱም ፍርድ ቤት እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ የአክሱም ሴት ተማሪዎች ሒጃብ እንዳይለብሱ የተጣለባቸው እገዳ እንዲነሳ ባለፈው ሳምንት ያሳለፉት ውሳኔ ባለመተግበሩ ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።

ሰልፉ “ሒጃብ ትለብሳለች ትምህርቷም ትማራለች” በሚል መሪ ቃል፣ በመቐለ ጎዳናዎች ከተካሔደ በኋላ በከተማዋ ማዕከል በኾነው ሮማናት አደባባይ ተጠናቋል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ፕሬዝዳንት ሸኽ አደም ዓብደልቃድር ጁሃር፣ “ከአንድ ሺሕ 400 ዓመታት በፊት መጠግያ ያጡ አማኞች ተቀብላ ባሰተናገደችው ትግራይ እንዲህ ማጋጡሙ አሳዛኝ ነው ብለዋል።

የሰልፈኞቹ ተወካዮች ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ጋራ ተወያይተዋል። አቶ ጌታቸው ለጥያቄው አፋጣኝ መፍትሄ ባለመሰጠቱ ይቅርታ ጠይቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG