በትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን የሚገኘው የኢሮብ ብሔረሰብ፣ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ረኀብ እንደተጠቃ የገለጹ ተወላጆች፣ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
የኢሮብ ልማት ማኅበር ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጸው፣ የብሔረሰቡ ግማሽ አካል በኤርትራ ኀይሎች እጅ እንደሚገኝ ጠቅሶ፣ በዚኽም የመበታተን አደጋ እንደተጋረጠበት አመልክቷል፡፡
በወረዳው የተከሠተውን ረኀብ እና የሰላም ዕጦት፣ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በማሳወቅ ሕዝቡ አስቸኳይ እገዛ እንዲደረግለት እየጣረ እንደሚገኝ፣ ማኅበሩ አስታውቋል፡፡
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናንት ጀነራል ጻድቃን ገብረ ትንሣኤ፣ የብሔረሰቡንና ሌሎች የክልሉን ተፈናቃይ ነዋሪዎች ችግር ለመፍታት፣ አስተዳደራቸው ከፌዴራሉ መንግሥት ጋራ እየተነጋገረ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡
ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም