በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉባኤ ያካሄዱ የህወሓት አመራሮች የጊዚያዊ ካቢኔ መግለጫ ተቃወሙ


ETHIOPIA-CONFLICT/UN
ETHIOPIA-CONFLICT/UN
ጉባኤ ያካሄዱ የህወሓት አመራሮች የጊዚያዊ ካቢኔ መግለጫ ተቃወሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:20 0:00

ጉባኤ ያካሄዱ የህወሓት አመራሮች ትላንት ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ባወጡት መግለጫ: የትግራይ ክልል የፀጥታ ሓይሎች በአስተዳደሩ ስር መሆን አይገባውም ሲሉ የክልሉን አስተዳደር ካቢኔ ውሳኔ እንደሚቃወሙ ገለፁ፡፡

"በአሁኑ ግዜ በህወሓት ውስጥ ክፍፍል እንዳለ ለማሳየት፣ በክልሉ አስተዳደር የቀረበው አገላለጽ ተቀባይነት የለውም" ያለው መግለጫቸው "ልዩነቱ ያለው ህወሓትን በማዳን የትግራይን ህዝብ ጥቅም ለማረጋገጥ በሚጥር ፓርቲ እና በሂደት ከትግል ወጥቶ ፓርቲውን እና ሰራዊቱን ለማፍረስ በሚንቀሳቀስ ቡድን መሃከል ነው" ሲል ጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል የጊዝያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ለወረዳዎች፣ ከተሞች እና ክፍለ ከተሞች ምክርቤቶች በፃፉት ደብዳቤ: "ህገወጥ ጉባኤ ያካሄደ ቡድን፣ ምክር ቤቶችን በመጠቀም ይቃወሙኛል ያላቸውን አመራሮች ከስልጣን እያወረደ እና ጥላሸት እየቀባ ነው፣ ይህ መቆም አለበት" ብለዋል፡:

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG