ዘንድሮ ግማሽ ሚልዮን የዶሮ ጫጩቶችን ወደ ሞዴል ገበሬዎች ለማዳረስ ተዘጋጅተዋል::
ይህንን ቁጥር በሚቀጥለው ዓመት ወደ አንድ ሚልዮን ከፍ ለማድረግ ማቀዳቸውን ገልፀው “በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እያንዳንዷ የትግራይ እናቶች ሰላሣ ዶሮዎች እንዲኖሯት እናስችላለን” ብለዋል ዴቪድ ኤልስ::
ትረንት ኮስቶቮስ “እኛ እየሠራን ያለነው በምሳሌነት የሚጠቀስ ማኅበረሰባዊ መዋዕለ-ነዋይን በተግባር ለማሣየት ነው” ይላሉ::
የመቀሌ እርሻ ለረጅም ዓመታት በሞያዊ ክፍተትና በአስተዳደራዊ አቅም ማነስ የሚፈለገውን ውጤት ሳያስመዘግብ መቆየቱን በዚህም መንግሥት በዓመት 15 ሺህ ዶሮዎችን ብቻ ያመርትበት እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል::