የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር “ምዕራብ ትግራይ ዞን” እያለ የሚጠራውና ከጦርነቱ ፍጻሜ በኋላ በዐማራ ክልል “የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን” ተብሎ ወደተቋቋመው አካባቢ፣ ተፈናቃዮችን መመለስ እንደሚጀመር፣ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ተናግረዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሌተናንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ በሰጡት መግለጫ፣ በክልሉ ተባብሰዋል በተባሉ ወንጀሎች ተጠያቂነትን ለማስፈን ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንደሚሠራም ገልጸዋል።
መድረክ / ፎረም