በትግራይ ክልል የጦርነት ተፈናቃዮች፣ “ይኣክል”(ይበቃል) በሚል መሪ ቃል ለሦስት ቀናት በመቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ፣ ዛሬ ኀሙስ ንጋት ላይ ተጠናቋል።
ሰልፈኞቹ፣ ትላንት ረቡዕ ባወጡት የአቋም መግለጫ፣ “የትግራይ ክልል መሪዎች ተፈናቃዮችን መመለስ ካልቻሉ ሥልጣናቸውን ይልቀቁ” በማለት ጠይቀዋል።
ይህንኑ መግለጫቸውን በጽሑፍ፣ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ እና ለህወሓት ሊቀ መንበር ዶር. ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል በአካል ቀርበው አስረክበዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም