በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለጋሾች ትግራይ ውስጥ ረሃብ አለ ይላሉ፤ መንግሥት ያስተባብላል


ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ
ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ

የትግራይ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸውን የሚገልፁ መግለጫዎች መሬት ላይ ያለውን እውነታ አያሳዩም ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአካባቢው መታረስ ከሚችለው መሬት 70 ከመቶው ለእርሻ ዝግጁ ሆኗል ያሉት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ይህ ደግሞ የከፋ ረሃብን እንደሚያስቀር ነው ያብራሩት።

የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ዛሬ ባወጧቸው መግለጫዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በከፋ ረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

350 ሺህ ዜጎች ደግሞ በከፋ ረሃብ እና ቸነፈር ላይ ይገኛሉ ሲል የዓለም ምግብ ፕሮግራም አመልክቷል። ተኩስ አቁምን ጨምሮ አመች ሁኔታዎች እንዲፈጠሩም ጥሪ አቅርቧል።

ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ለትግራይ ክልል ሰብአዊ እንቅስቃሴ የሚሆን የ181 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርጋለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ለጋሾች ትግራይ ውስጥ ረሃብ አለ ይላሉ፤ መንግሥት ያስተባብላል
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:00 0:00


XS
SM
MD
LG