በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት ትግራይ ውስጥ ተኩስ አቁም አወጀ


ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ
ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ

የኢትዮጵያ መንግሥት ትግራይ ውስጥ የተናጠልና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁም አውጇል። በሌላ በኩልም ህወሓት መቀሌ መግባቱንና ከተማዪቱን መቆጣጠሩን ማምሻውን ልሳኑ በሆነው ራዲዮ ‘ድምፅ ወያነ’ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ የትግራይ ክልልን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በኢትዮጵያውያንና በኢትዮጵያ ወዳጆች ሲቀርቡ የነበሩ የመፍትሔ ሃሳቦችን ሲያጤን መቆየቱንና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተከታታይ ያቀረበውን ጥያቄ ከተለያየ አቅጣጫ መመልከቱን ጠቁሞ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ጥያቄ በአዎንታዊነት መቀበሉን አስታውቋል።

ጥያቄው ከመቅረቡ በፊት በተለያየ ጊዜ ከክልሉ ተወላጆች፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት የተደረገበት መሆኑን መግለጫው አመልክቶ በስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከመቸውም በላይ ለሃገራችን ሰላም የሰጡትን ልዩ ትኩረት ከግምት ውስጥ ገብቷል” ብሏል።

ባለፈው ዓመት የአምበጣ መንጋ በስፋት ያጠቃው ክልል መሆኑንና የግብርና ሰብል ምርት በበቂ ሁኔታ አላገኝም ያስታወሰው የኢትዮጵያ መንግሥት መግለጫ ይሄንን ክረምት ያለ እርሻ ሥራ የሚያሳልፍ ከሆነ ለገበሬው በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚሆንበት አመልክቷል።

መግለጫው በተጨማሪም በዘረዘራቸው ሌሎች ምክንያቶችም ይህ የእርሻ ወቅት እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚቆይ ያለቅድመ ሁኔታ በሰብአዊነት ላይ የተመሠረተ በተናጠል የተኩስ አቁም ከዛሬ ከሰኔ 21 ቀን 2013 ጀምሮ መንግሥት ማወጁን አስታውቋል።

ሁሉም የፌዴራልና የክልል ሲቪልና ወታደራዊ ተቋማት፣ ከመንግሥት በሚሰጣቸው ዝርዝር አፈጻጸም መሠረት ይሄን የተኩስ አቁም እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ መታዘዛቸውንም መግለጫው አክሎ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG