ላለፉት ዐሥር ወራት የርዳታ እህል እንዳልተሰጣቸው የገለጹ፣ በትግራይ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች፣ በእጅጉ መቸገራቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡
ለደኅንነታቸው በመስጋት ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አስተያየት ሰጭዎች፣ ከሥፍራው በስልክ እንደገለጹልን፣ በማይ ዓይኒ እና በዓዲ ሓሩሽ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ፣ 1ሺሕ700 ስደተኞች ይኖራሉ፡፡ ኾኖም፣ በመጠለያ ጣቢያዎቹ፣ መሠረታዊ አገልግሎት ባለመኖሩ፣ ለከባድ ችግር እንደተጋለጡ አስታውቀዋል፡፡ በሕክምና ዕጦት ምክንያት፣ በቅርቡ የ20 ሰዎች ሕይወት ማለፉንም ገልጸዋል፡፡
ስለ ጉዳዩ፣ ከኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት፣ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር/UNHCR/ በበኩሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በኢሜይል በሰጠው ምላሽ፣ “ስደተኞቹ፣ በዚያ አካባቢ ኾነው አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ አስቀድመን ነግረናቸዋል፡፡ አሁንም ወደ ቦታው መግባት አንችልም፤” በማለት ገልጿል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም