በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል የታሰሩ የመከላከያ አባላት ጉዳይ ቤተሰቦቻቸውን አሳስቧል


በትግራይ ክልል የታሰሩ የመከላከያ አባላት ጉዳይ ቤተሰቦቻቸውን አሳስቧል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:15 0:00

በትግራይ ክልል የታሰሩ የመከላከያ አባላት ጉዳይ ቤተሰቦቻቸውን አሳስቧል

የትግራይ ክልልን መነሻ ባደረገው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት በተለያዩ አጋጣሚዎች ተይዘው ከሰላም ስምምነቱ በኋላም ያልተለቀቁ ምርኮኛ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ደኅንነት እንደሚያሳስባቸው የታሳሪ ቤተሰቦች ገለጹ፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በቅርቡ 212 ምርኮኛ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን መፍታቱንና የቀሪዎቹም ጉዳይ “በአጭር ጊዜ ውስጥ” መፍትሔ እንደሚያገኝ አስታውቆ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ(ኢሰመጉ)፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በእስር ላይ ያሉ ቀሪ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአስቸኳይ የሚፈቱበትን ኹኔታ እንዲያመቻች ጠይቋል፡፡ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG