በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ በጦርነቱ ወቅት የወጡ ሕጎች እንዲሻሩ ተጠየቀ


በትግራይ በጦርነቱ ወቅት የወጡ ሕጎች እንዲሻሩ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:34 0:00

በትግራይ በጦርነቱ ወቅት የወጡ ሕጎች እንዲሻሩ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል፣ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ከመፈረሙ በፊት፣ ህወሓት ልዩ ልዩ የአስቸኳይ ጊዜ ሕጎች ደንግጎ እንደነበር ያስታወሰው ፓርቲው፣ ኾኖም ሒደቱ፣ ሕጋዊነትን የተከተለ እንዳልነበረና የሕጎቹ ይዘትም፣ ከክልሉ እና ከፌዴራሉ ሕገ መንግሥቶች ጋራ እንደማይጣጣም ገልጿል፡፡ ሕጎቹ ሥራ ላይ በዋሉባቸው ጊዜያትም፣ የተለያዩ ችግሮች ማስከተላቸውን ፓርቲው አመልክቷል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ እነዚኽን ሕጎች እንዲሽራቸው የጠየቀው ፓርቲው፣ ካልሆነ ግን፣ ጉዳዩን ወደ ሕገ መንግሥት አጣሪ አካል እንደሚወሰደው፣ የፓርቲው የሕግ እና የሥነ መንግሥት ክፍል ሓላፊ አቶ ተስፋኣለም በርኸ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ፣ ከትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡ ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን አንድ ከፍተኛ የሥራ ሓላፊ ግን፣ ቢሮው ሕጎቹን እየሻረ፣ ወደ መደበኛው የፍትሕ አሠራር ለመግባት እንቅስቃሴ መጀመሩንና በሕጎች ተከሠው ስለተፈረደባቸው ሰዎችም፣ የባለሞያዎች ቡድን ተቋቁሞ ጥናት እያደረገ እንደኾነ ጠቁመዋል፡፡

XS
SM
MD
LG