በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ


በትግራይ ክልል ደቡብ፣ ማዕከላዊና ምዕራብ ዞናች በሚገኙ ከተሞች ትናንትናው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

በትግራይ ክልል ደቡብ፣ ማዕከላዊና ምዕራብ ዞናች በሚገኙ ከተሞች ትናንትናው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
በቅርብ ግዜ በክልልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የተሰጠ መግለጫ እንደግፋለን፣ ብሄር መሰረት ያደረገ ጥቃት እንቃወማለን፣ ሕገ መንግሥት ይከበር የሚሉና ሌሎች መፈክሮች የተደመጠበት ሰልፎች ነበሩ።
በምዕራባዊና ደቡባዊ ዞኖች በነበሩ ሰልፎች በማንነት ስም የሚቀርብ ጥያቄ እኛ አይወክልም የሚል መፈክርም ቀርበዋል።
በአላማጣ ከተማ ሰልፉ ከመካሄዱ አንድ ቀን በፊት በ፫ ቦታዎች ቦምቦች የተወረወሩ ሲሆን በሰው ይህን ንብረት ያደረሰው ጉዳት እንደሌለና ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የከተማዋ አስተዳደር አስታውቋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በትግራይ ክልል የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:19 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG