በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ዛሬ በይፍ በተጀመረው፣ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ ወደ ኅብረተሰቡ መልሶ የማዋሐድና የማቋቋም ሥራ 320 የቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቃቸውን አስረክበው፣ ማሰልጠኛ ተቋማት ገቡ። በማሰልጠኛ ተቋማቱም ስድስት ቀናትን በሥልጠና እንደሚያሳልፉ፣ በዛሬው ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የብሔራዊ ተሐድሶ ኮምሽን ምክትል ኮምሽነር ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያ ተናግረዋል።
መድረክ / ፎረም