በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል አሠቃቂ የሴቶች ጥቃት የሲቪል ማኅበረሰቦች መንግሥትን ወቀሱ


መቀሌ ከተማ
መቀሌ ከተማ

በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያ፣ እገታ እና ጾታዊ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም በጋራ መግለጫቸው የጠየቁ 27 ክልላዊ የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማት፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ “በችግሩ ልክ ተጠያቂነትን እያረጋገጠ አይደለም፤” ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

በትግራይ ክልል አሠቃቂ የሴቶች ጥቃት የሲቪል ማኅበረሰቦች መንግሥትን ወቀሱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:42 0:00

ተቋማቱ የፖሊስን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በመግለጫቸው እንዳመለከቱት፣ ባለፉት 11 ወራት ውስጥ በመቐለ ከተማ ብቻ፣ በ12 ሴቶች ላይ ግድያ እና በ80 ሴቶች ላይ ደግሞ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ተፈጽመዋል።

በጉዳዩ ላይ፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ምላሽ እና ማብራርያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ይኹንና፣ በክልሉ ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም ለመጠየቅ፣ በቅርቡ በመቐለ ከተማ ሰልፍ ለወጡ ሴቶች ምላሽ የሰጡት፣ የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሓዱሽ ተስፋ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የሴቶችን ጥቃት ጉዳይ፣ “በይደር የሚያቆየው ነገር አይኾንም፤ የርምጃውም ውጤት በቅርቡ መታየት ይጀምራል፤” ሲሉ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG