በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ ለትግራይ ክልል አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደረግ ጠየቀ


የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ ለትግራይ ክልል አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደረግ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:52 0:00

የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ ለትግራይ ክልል አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደረግ ጠየቀ

በትግራይ ክልል ባለፈው ክረምት በኣዝርዕት ከተሸፈነ መሬት፣ 37 በመቶ ምርት ብቻ እንደተገኘ የክልሉ ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ገለጸ።

ከፍተኛ የምርት መቀነስ የታየው፣ በድርቅ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ምክንያት እንደኾነ፣ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዓለም ብርሃን ሃሪፈዮ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል ጉብኝት ያደረገው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ደግሞ፤ በድርቅ ምክንያት 49 በመቶ የክልሉ መሬት አለመታረሱን ገልጾ፣ መንግሥት እና የተራድኦ ተቋማት ችግረኛ ወገኖችን እንዲያግዙ ጥሪ አቅርቧል።

የትግራይ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ፣ ከ4ነጥብ5 ሚሊዮን በላይ የክልሉ ሕዝብ፣ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ፈላጊ እንደኾነ አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG