በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል ለተባባሱ የወንጀል ተግባራት መፍትሔ እንዲሰጥ ተጠየቀ


በትግራይ ክልል ለተባባሱ የወንጀል ተግባራት መፍትሔ እንዲሰጥ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:34 0:00

በትግራይ ክልል ለተባባሱ የወንጀል ተግባራት መፍትሔ እንዲሰጥ ተጠየቀ

በትግራይ ክልል፣ በተለያዩ መነሻዎች እየተፈጠሩ ያሉ የጸጥታ ችግሮች መፍትሔ እንዲሰጣቸው፣ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩ ነዋሪዎች ጠይቀዋል፡፡

በዓድዋ ከተማ፣ ባለፈው መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በአጋቾች የተያዘች ልጃቸውን ለማስለቀቅ፣ ፖሊስ ተገቢውን ክትትል አለማድረጉን ወላጅ አባቷ ወቅሰዋል፡፡

የከተማዋ ፖሊስ በበኩሉ፣ አዳጊዋን ታጋች ለማግኘት ኅብረተሰቡን በማስተባበር የሚቻለውን ጥረት እያደረገ መኾኑን ገልጿል፡፡

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ዓረና ለሉዓላዊነት እና ዴሞክራሲ ፓርቲ በበኩሉ፣ በክልሉ በተለይ በወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ላይ “ሥርዓት አልበኝነት ሰፍኗል፤” ብሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የመሬት እና ማዕድን ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

የትግራይ ክልል የገቢ እና ሀብት ማሰባሰብ ሰክሬታርያት ሓላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎድፋይ፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ፣ ከወረዳ እና ከዞን አመራሮች ጋራ ባካሔዱት ውይይት፣ በክልሉ በመሬት፥ በመዓድን፥ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሌሎች ዘርፎች የተፈጸሙ ምዝበራዎች ጥናት መቅረቡን ጠቅሰው፣ “ርምጃ ወደ መውሰድ እንገባለን፤” ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG