በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መግለጫ


የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት የሁለቱም ህዝቦች ሰላም በዘላቂነት ለመፍታት እያሳዩት ያለ ዝግጁነትና ተነሳሽነት ያደንቃል ብሏል የትግራይ ኮሙኒኬሽንስ ቢሮ ያወጣው መግለጫ።

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት የሁለቱም ህዝቦች ሰላም በዘላቂነት ለመፍታት እያሳዩት ያለ ዝግጁነትና ተነሳሽነት ያደንቃል ብሏል የትግራይ ኮሙኒኬሽንስ ቢሮ ያወጣው መግለጫ።

በተለይ የኤርትራ ህዝብ ለ20 ዓመታት የዘለቀውን ሁኔታ በመፍታት የኢትዮጵያና የኤርትራ ወንድማማችንት እንዱሁም ወዳጅነት ለማጠናከር ያሳየው ፍላጎት፣ ጉጉትና ፍቅር እጅግ የሚያስደስትና ብሩህ ተስፋ እንዳለም የሚገለፅ ነው፡፡ በመሆኑም የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለኤርትራ ህዝብ ያለው ወንድማዊ አድናቆት ከፍ ያለ መሆኑን መግለፅ ይፈልጋል ሲልም አክሏል፡፡

የኢትዮ-ኤርትራ ሁኔታን በዘላቂነት ለመፍታት በሚደረገው ሁሉን-አቀፍ ጥረት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት እና የትግራይ ህዝብ ከኤርትራ ህዝብ ጎን እንደሚቆሙ እያረጋገጡ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦችም የተጀመረውን ሰላም የማረጋገጡን ሥራ ይበልጥ ለማጠናከር በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀጥተኛ የሆነ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በመጀመር ወንድማማችነታቸውንና ወዳጅነታቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪውን ያቀርባል ይላል የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያወጣው መግለጫ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG