በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮ-ቴሌኮም በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች አገልግሎት ጀመረ


የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ

በትግራይ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎት እንደገና መጀመሩን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታውቋል።

ያጋጠሙ ጉዳቶችን በመጠገን እና መልሶ በማቋቋም እንዲሁም አማራጭ የሃይል አቅርቦቶችን በመጠቀም ላይ መሆናቸውን የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ለአሜሪካ ድምፅ አብራርተዋል።

አገልግሎቱ በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሁመራ፣ በሽራሮ፣ በማይፀብሪ እና በማይካድራ በከፊል በአላማጣ ደግሞ ሙሉ በሙሉ መጀመሩንም ጠቁመዋል።

የመቀሌው የቴሌኮም መሰረተ ልማት መጎዳት አለመጎዳቱን የሚያጠና ቡድን መላኩን እና እስከ ነገ ድረስ ውጤቱ እንደሚታወቅም ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ኢትዮ-ቴሌኮም በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች አገልግሎት ጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:09 0:00


XS
SM
MD
LG