ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋራ ተያይዞ፣ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው የተባሉ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሠረት እንዲፈቱ ቤተሰቦቻቸው ጥሪ አቀረቡ፡፡
ለደኅንነታቸው በመስጋት ማንነታቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁን አስተያየት ሰጭዎች፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የኾኑ ቤተሰቦቻቸው፣ ከሦስት ዓመታት በላይ ለኾነ ጊዜ በልዩ ልዩ ማረሚያ ቤቶች ታስረው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
“ሂዩማን ራይትስ ፈርስት” የተባለ ኢትዮጵያዊ የመብት ተሟጋች በበኩሉ፣ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም፣ በ16 ማረሚያ ቤቶች 154 የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ታስረው እንደሚገኙ በምርመራ ማረጋገጡን ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡
መድረክ / ፎረም