በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአቶ ገብሩ አሥራት የኢትዮጵያ ግምገማ


አቶ ገብሩ አሥራት
አቶ ገብሩ አሥራት

የግንቦት ሃያን 29ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ጊዜ እጅግ አሳሳቢ መሆኑንና በኢህአዴግ ዘመን “ተጨብጠው ነበር” ያላቸው ፖለቲካዊ፣ ምጣኔኃብታዊ፣ ማኅበራዊና ዓለም አቀፍ ስኬቶች መቀልበሳቸውን፤ አልያም እያሽቆለቆሉ መሆናቸውን በመግለፅ በከበዱ ቃላትና አቀራረብ ተችቷል።

“ሃገሪቱ ገደል አፋፍ ላይ ትገኛለች” ብሏል።

ይህ መግለጫና ፌደራል መንግሥቱም የሰጡት ምላሽ በምልዓት ተዘግበዋል።

ለመሆኑ በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችና ህዝብስ ምን ይላሉ? ማነጋገር ጀምረናል። የትግራይ ሕዝብ ያለበት የድኅነት ክብደት “ከማንኛውም ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የባሰ ነው፣ የበረታ ጭቆናም አለበት” ሲሉ የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት አመራር አባላት አቶ ገብሩ አሥራት እና አቶ አምዶም ገብረሥላሴ ተናግረዋል።

ሁለቱም ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የግንቦት ሃያን 29ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ያወጣውን መግለጫ “የተጋነነ” ብለውታል።

ከዚህ መግቢያ ጋር የተያያዘው ከአቶ ገብሩ አሥራት ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ የተካሄደው ከጥቂት ሣምንታት በፊት ነበር። በራዲዮ ዝግጅታችን ቀደም ሲል በከፊል ቢስተናገድም ሙሉው ቃለ ምልልስ በገፆቻችን ላይ ሳይወጣ ቆይቷል። ያዳምጡት።

በነገራችን ላይ፣ የትግራይን ክልላዊ መንግሥት ተጨማሪ ማብራሪያና ሃሣብ ለመጠየቅ ከክልሉ ፕሬዚዳንት አንስቶ በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ ባለሥልጣናትን ለማግኘት በስልክና በቴክስት መልዕክት በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሣካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአቶ ገብሩ አሥራት የኢትዮጵያ ግምገማ
please wait

No media source currently available

0:00 1:06:01 0:00


XS
SM
MD
LG