በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለትግራይ ክልል የእርዳታ አቅርቦት ጉዳይ


ሳማንታ ፓወር
ሳማንታ ፓወር

በትግራይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከዚህ ሳምንት በኋላ የምግብ አቅርቦት ማድረስ የማይቻልበት ደረጃ ላይ መደረሱን የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ /ዩኤስኤአይዲ/ ገለጸ።

ይህ የሆነው የምግብ እጥረት በመኖሩ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ሰብዓዊ ዕርዳታ እና ሠራተኞችን እንዲሁም እርዳታ የጫኑ መኪኖችን እና የአየር ትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችን እያደናቀፈ በመሆኑ ነው ሲሉ የተቋሙ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ከሰዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ዘርፍ ኃላፊ ቢል ለኔ ስዩም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ፣ ወደ ክልሉ ለሚገቡ የእርዳታ አገልግሎቶች መንግሥት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩን እንደቀጠለ በመግለጽ ክሱን አጣጥለዋል፡፡

ኦቻ በበኩሉ በየቀኑ የሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ 100 መኪኖች ወደ ትግራይ እንዲገቡ ቢጠበቅም በቀን የፍተሸ ሂደት የሚከናወነው ግን ለ30 መኪኖች ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡ እናም የኢትዮጵያ መንግሥት ሂደቱን ማፋጠን የሚቻልበት እርምጃ እንዲወስድ ሁለቱ ተቋማት ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

ለትግራይ ክልል የእርዳታ አቅርቦት ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:06 0:00


XS
SM
MD
LG