በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሪቶርያው ስምምነት ፍሬዎች እና ያልተሟሉ ተስፋዎች


የፕሪቶርያው ስምምነት ፍሬዎች እና ያልተሟሉ ተስፋዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:53 0:00

የፕሪቶርያው ስምምነት ፍሬዎች እና ያልተሟሉ ተስፋዎች

በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል፣ ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት፣ በደቡብ አፍሪካ - ፕሪቶርያ ከተፈረመ ነገ፣ ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. አንድ ዓመት ይኾነዋል።

የትግራይ ክልልን መነሻ አድርጎ ለኹለት ዓመታት ያህል የተካሔደው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቆሙና ተቋርጠው የነበሩ መሠረታዊ አገልግሎቶች ዳግም መጀመራቸው፣ የሰላም ስምምነቱ ፍሬዎች እንደኾኑ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው በክልሉ የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ ነዋሪዎች እና የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገልጸዋል።

የተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው አለመመለስ፣ የውጭ ኃይሎች እና ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውጭ የኾኑ ታጣቂዎች ከክልሉ አለመውጣት፣ እንዲሁም የሰብአዊ ድጋፍ መቋረጥ ደግሞ፣ በስምምነቱ መሠረት ሊተገበሩ ያልቻሉ ጉዳዮች እንደኾኑ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG