በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ እና የዓፋር ክልሎች ፕሬዝዳንቶች ውይይት ተስፋ እንዳሳደረባቸው ተፈናቃዮች ገለፁ


የትግራይ እና የዓፋር ክልሎች ፕሬዝዳንቶች ውይይት
የትግራይ እና የዓፋር ክልሎች ፕሬዝዳንቶች ውይይት
የትግራይ እና የዓፋር ክልሎች ፕሬዝዳንቶች ውይይት ተስፋ እንዳሳደረባቸው ተፈናቃዮች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:50 0:00

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ባለፈው ረቡዕ መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ/ም በዓፋር ክልል ያደረጉት ጉብኝትና ተደረሰባቸው የተባሉ ስምምነቶች ተስፋ እንዳሳደሩባቸው በመቀሌ አካባቢ የተጠለሉ የአብዓላ ተፈናቃዮች ተናግረዋል።

ችግር ውስጥ እንደሚገኙ የገለፁት ተፈናቃዮቹ ስምምነቱ ቶሎ እንዲተገበርም ጠይቀዋል።

የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፣ ባለፈው ረቡዕ በአፋር ያደረጉት ጉብኝት ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በኋላ የመጀመሪያ ነው።

አቶ ጌታቸው በፌስቡክ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ከዓፋር ክልል ፕሬዝዳንት አወል አርባ ጋራ ባደረጉት ውይይት ፣ በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉትን በመመለስ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማስጀመር እንዲሁም ሰላም፣ ፀጥታና ልማትን በጋራ በማረጋገጥ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG